Spoort

በኳታሩ ዓለም ዋንጫ ዛሬ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደረጉት ጨዋታ ይጠበቃል


ቀን 7 ሰዓት ዌልስ ከኢራን በምድብ 2 የሁለተኛ ዙር ጨዋታ በአህመድ ቢን አሊ ስቴዲየም የሚገናኙ ይሆናል።በምድቡ ደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች አሸንፈው የማለፍ ተስፋቸውን ለማለምለም የሚፋለሙ ይሆናል።
በመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸው ኢራን በኢንግሊዝ 6 ለ 2 ስትሸነፍ ዌልስ ከአሜሪካ ጋር 1 ለ 1 ተለያይታ ነጥብ መጋራቷ ይታወሳል። በዌልስ በኩል ጉዳት ላይ ያሉት ሃሪ ዊልሰን፣ ኢታን አምፓዱ እና ኒኮ ዊሊያምስ መሰለፍ አጠራጣሪ ነው። ከኢንግሊዝ ጋር በነበረው ግጥሚያ ጉዳት የገጠመው የኢራኑ ግብ ጠባቂ አሊረዛ ቤይራንቫንድ የመሰለፉ ጉዳይ አልተረጋገጠም።ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በፊት 1 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ዌልስ ማሸነፍ ችላ ነበር።
ቀጥሎ ቀን 10 ሰዓት ላይ በምድብ 1 ሁለተኛ ዙር በሚደረገው ጨዋታ አስተናጋጇ ኳታር ከሴኔጋል በአል-ቱማማ ስቴዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።ሁለቱም ቡድኖች የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በሽንፈት የጀመሩ ሲሆን ከሽንፈታቸው ለማገገም እና አሸንፈው ለመውጣት ጠንካራ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።በሴኔጋል በኩል ቼኩ ኩያቴ፣ አማዱ ዲያሎ እና ባሎ ቱሬ በጉዳት ላይሰለፉ ይችላሉ።በአንጻሩ የኳታር ብሄራዊ ቡድን ምንም አይነት የጉዳት ዜና አልተሰማበትም።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በምድብ 1 የመጀመሪያ ጨዋታቸው ድል የቀናቸው ኔዘርላንድ እና ኢኳዶር በካሊፋ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።በኢኳዶር በኩል ወሳኙ አጥቂ ኢነር ቫሌንሺያ በጉልበት ጉዳት የመሰለፉ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል።ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ የተገናኙት ቡድኖቹ በአንዱ አቻ ሲለያዩ በአንዱ ደሞ ኔዘርላንድ ማሸነፍ ችላለች።
በእለቱ ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ኢንግሊዝ ከአሜሪካ በምድብ ሁለት 2ኛ ዙር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።በርከት ያሉ የጉዳት ዜናዎች ከኢንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የተሰማ ሲሆን ካሉም ዊልሰን፣ ሃሪ ኬን እና ጄምስ ማዲሰን መሰለፋቸው አጠራጣሪ ሲሆን ሃሪ ማጓየር ደግሞ ለተወሰኑ ቀናት በጉዳት ቡድኑን እንደማያገለግል ተረጋግጧል።
በአሜሪካ በኩል እንዲሁ የዌስተን ማክኬኒ እና የኑስ ሙሳ መሰለፍ አልተረጋገጠም።ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በፊት 5 ያህል ጊዜ ተገናኝተው ኢንግሊዝ አራቱን ስታሸንፍ በአንዱ ጨዋታ ደሞ አቻ ወጥተዋል።
ጨዋታዎቹን በኢቲቪ መዝናኛ – HD: ETHIOSAT NSS-1257E, Frequency 11105MHz, Symbol Rate 45000, Polarization Horizontal በማድረግ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬድዮ እና ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ላይ ጨዋታዎቹን እንድትከታተሉ ጋብዘንዎታል።

Leave a comment

Design a site like this with WordPress.com
Get started